5. ስለዚህ ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ፤ለእነርሱም እናገራለሁ፤በእርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድ፣የአምላካቸውንም ሕግ ያውቃሉና።”ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ ያው እንደዚያው ቀንበሩን ሰብረዋል፤እስራቱንም በጥሰዋል።
6. ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰባብራቸዋል፣የበረሓ ተኵላም ይቦጫጭቃቸዋል፤ብቅ የሚለውን ሰው ሁሉ ለመገነጣጠል፣ነብር በከተሞቻቸው ዙሪያ ያደባል፤ዐመፃቸው ታላቅ፣ክሕደታቸው ብዙ ነውና።
7. “ታዲያ፣ እንዴት ይቅር ልልሽ እችላለሁ?ልጆችሽ ትተውኛል፤እውነተኛውን አምላክ ትተው አማልክት ባልሆኑት ምለዋል፤እስኪጠግቡ ድረስ መገብኋቸው፤እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ወደ ጋለሞቶችም ቤት ተንጋጉ።
8. እንደ ተቀለበ ብርቱ ድንጒላ ፈረስ ሆኑ፤እያንዳንዱም የሌላውን ሚስት ተከትሎ አሽካካ።
9. ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀጣቸውምን?”ይላል እግዚአብሔር።“እኔ ራሴ እንደዚህ ዐይነቱን ሕዝብ፣አልበቀልምን?