20. “በያዕቆብ ቤት ይህን አሰሙ፣በይሁዳም እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤
21. እናንት ዐይን እያላችሁ የማታዩ፣ጆሮ እያላችሁ የማትሰሙ፣ሞኞችና የማታስተውሉ ሰዎች ይህን ስሙ፤
22. ልትፈሩኝ አይገባችሁምን?” ይላል እግዚአብሔር፤“በእኔ ፊት ልትንቀጠቀጡስ አይገባምን?ለዘላለም ዐልፎት መሄድ እንዳይችል፣አሸዋን ለባሕር ድንበር አደረግሁ፤ማዕበሉ እየጋለበ ቢመጣ ከዚያ አያልፍም፤ሞገዱ ቢጮኽም ሊያቋርጠው አይችልም።
23. ይህ ሕዝብ ግን የሸፈተና እልከኛ ልብ አለው፤መንገድ ለቆ ሄዶአል፤
24. በልባቸውም፣‘የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚያዘንበውን፣መከርን በወቅቱ የሚያመጣልንን፣አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ’ አላሉም።