ኤርምያስ 48:23-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. በቂርያታይም፣ በቤት ጋሙልና በቤትምዖን ላይ፣

24. በቂርዮትና በባሶራ ላይ፤በሩቅና በቅርብ፣ ባሉት በሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቶአል።

25. የሞዓብ ቀንድ ተቈርጦአል፤እጁም ተሰባብሮአል፤”ይላል እግዚአብሔር።

26. “እግዚአብሔርን ንቆአልና፣ሞዓብን በመጠጥ አስክሩት።ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለል፤ለመዘባበቻም ይሁን።

ኤርምያስ 48