ኤርምያስ 47:5-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ጋዛ በማዘን ራሷን ትላጫለች፣አስቀሎና አፏን ትይዛለች።በሜዳማ ስፍራ የምትገኙ ትሩፋን ሆይ፤እስከ መቼ ሰውነታችሁን ትቧጥጣላችሁ?

6. “ ‘የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ፤የማታርፈው እስከ መቼ ነው?ወደ ሰገባህ ተመልሰህ ግባ፤ጸጥ ብለህ ተቀመጥ’ ትላላችሁ።

7. ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀሎናንና የባሕሩን ዳርቻ፣እንዲወጋ ሲያዝዘው፣እንዲፈጽመውም ትእዛዝ ሲሰጠው፣እንዴት ማረፍ ይችላል?”

ኤርምያስ 47