ኤርምያስ 31:30-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. ነገር ግን፣ እያንዳንዱ በገዛ ኀጢአቱ ይሞታል፤ ጐምዛዛ የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ የራሱን ጥርስ ይጠርሳል።

31. “ከእስራኤል ቤትና፣ከይሁዳ ቤት ጋር” ይላል እግዚአብሔር፤“አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት፣ጊዜ ይመጣል።

32. ከግብፅ አወጣቸው ዘንድ፣እጃቸውን ይዤ በመራኋቸው ጊዜ፣ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ኪዳንአይደለም፤የእነርሱ ባልገ ሆኜ ሳለሁ፣ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና።”ይላል እግዚአብሔር።

33. “ነገር ግን ከዚያ ጊዜ በኋላ፣ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር፤“ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤በልባቸውም እጽፈዋለሁ።እኔ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

ኤርምያስ 31