ኤርምያስ 31:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ካህናቱን አትረፍርፌ እባርካለሁ፤ሕዝቤም በልግስናዬ ይጠግባል፤”ይላል እግዚአብሔር።

15. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ዋይታና መራራ ልቅሶ፣ከራማ ተሰማ፤ልጆቿ የሉምና፣ራሔል አለቀሰች፤መጽናናትም እንቢ አለች።”

16. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ድምፅሽን ከልቅሶ፣ዐይኖችሽንም ከእንባ ከልክይ፤ድካምሽ ያለ ዋጋ አይቀርምና፤”ይላል እግዚአብሔር።“ከጠላት ምድር ይመለሳሉ፤

17. ስለዚህ ወደ ፊት ተስፋ አለሽ”ይላል እግዚአብሔር።“ልጆችሽ ወደ ገዛ ምድራቸው ይመለሳሉ።

18. “የኤፍሬምን የሲቃ እንጒርጒሮ በእርግጥ ሰምቻለሁ፤‘እንዳልተገራ ወይፈን ቀጣኸኝ፤እኔም ተቀጣሁ።አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና፣መልሰኝ፤ እኔም እመለሳለሁ።

ኤርምያስ 31