ኤርምያስ 20:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. “ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል” ብሎ፣ለአባቴ የምሥራች የነገረ፣ደስ ያሰኘውም ሰው የተረገመ ይሁን።

16. ያ ሰው እግዚአብሔር ሳይራራ፣እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን፤በማለዳ ዋይታን፣በቀትርም የጦርነትን ውካታ ይስማ፤

17. እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ፣ማሕፀንም ሰፊ የዘላለም ማደሪያዬ እንዲሆን፣ከማሕፀንም ሳልወጣ አልገደለኝምና።

18. ችግርና ሐዘንን ለማየት፣ዘመኔንም በውርደት ለመፈጸም፣ለምን ከማሕፀን ወጣሁ?

ኤርምያስ 20