ኤርምያስ 17:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ልጆቻቸው እንኳ ሳይቀሩ፣በለመለሙ ዛፎች ሥር፣ከፍ ባሉ ኰረብቶችም ላይ ያሉትን፣መሠዊያቸውንና አሼራ የተባለችውን ጣዖት ምስል ያስባሉ።

3. በአገርህ ሁሉ ከተፈጸመው ኀጢአት የተነሣ፣በምድሪቱ ያለህ ተራራዬ፣ሀብትህንና ንብረትህን ሁሉ፣መስገጃ ኰረብቶችህንም ጭምር፣ለብዝበዛ አደርገዋለሁ።

4. በገዛ ጥፋትህ፣የሰጠሁህን ርስት ታጣለህ፤በማታውቀውም ምድር፣ለጠላቶችህ ባሪያ አደርግሃለሁ፤ለዘላለም የሚነደውን፣የቍጣዬን እሳት ጭረሃልና።”

5. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በሰው የሚታመን፣በሥጋ ለባሽ የሚመካ፣ልቡንም ከእግዚአብሔር የሚያርቅ የተረገመ ነው።

ኤርምያስ 17