20. እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፋታችንን ዐውቀናልና፤የአባቶቻችንን በደል ተረድተናልና፤በእርግጥም በአንተ ላይ ኀጢአት ሠርተናል።
21. ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፤የክብርህንም ዙፋን አታዋርድ።ከእኛ ጋር የገባኸውን ኪዳን አስብ፤አታፍርሰውም።
22. ከአሕዛብ ከንቱ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለን?ሰማያትስ በራሳቸው ማካፋት ይችላሉን?አይ! አይችሉም፣ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ነህ፣ስለዚህም ተስፋችን በአንተ ላይ ነው።