ኢዮብ 6:20-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. እርግጠኞች ሆነው ስለ ነበር ተሰቀቁ፤እዚያ ደረሱ፣ ግን ዐፈሩ።

21. አሁንም እናንተ እንደዚያ ሆናችሁብኝ፣መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ።

22. ለመሆኑ፣ ‘ስለ እኔ ሆናችሁ አንድ ነገር ስጡልኝ፣በዕዳ የተያዘብኝንም በሀብታችሁ አስለቅቁልኝ!’ ብያለሁን?

23. ወይስ፤ ‘ከጠላት አስጥሉኝ፤ከጨካኝም እጅ ተቤዡኝ’ አልኋችሁን?

24. “አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ፤ምኑ ላይ እንደ ተሳሳትሁ ጠቍሙኝ።

25. የቅንነት ቃል ምንኛ ኀያል ነው!የእናንተ ክርክር ግን ምን ፋይዳ አለው?

26. የተናገርሁትን ለማረም፣ተስፋ የቈረጠውንም ሰው ቃል እንደ ነፋስ ለመቍጠር ታስባላችሁን?

27. በድኻ አደጉ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁን?ወይስ ወዳጃችሁን ትሸጣላችሁን?

28. “አሁን ግን ፈቃዳችሁ ቢሆን ወደ እኔ ተመልከቱ፤ፊት ለፊት እዋሻችኋለሁን?

29. መለስ በሉ፤ ፍርደ ገምድል አትሁኑ፤ጽድቄ ጸንታ ቆማለችና መለስ ብላችሁ አስተውሉ።

ኢዮብ 6