ኢዮብ 5:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እርሱ ከስድስት መቅሠፍት ይታደግሃል፤በሰባተኛውም ጒዳት አያገኝህም።

20. በራብ ጊዜ ከሞት፣በጦርነትም ከሰይፍ ያድንሃል።

21. ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፤ጥፋት ሲመጣም አትፈራም።

22. በጥፋትና በራብ ላይ ትሥቃለህ፤የምድርንም አራዊት አትፈራም።

ኢዮብ 5