ኢዮብ 5:18-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. እርሱ ያቈስላል፤ ይፈውሳል፤እርሱ ይሰብራል፤ በእጁም ይጠግናል፤

19. እርሱ ከስድስት መቅሠፍት ይታደግሃል፤በሰባተኛውም ጒዳት አያገኝህም።

20. በራብ ጊዜ ከሞት፣በጦርነትም ከሰይፍ ያድንሃል።

21. ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፤ጥፋት ሲመጣም አትፈራም።

22. በጥፋትና በራብ ላይ ትሥቃለህ፤የምድርንም አራዊት አትፈራም።

23. ከሜዳ ድንጋዮች ጋር ትዋዋላለህና፤የዱር አራዊትም ከአንተ ጋር ይስማማሉ።

ኢዮብ 5