ኢዮብ 41:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ሌዋታንን በመንጠቆ ልታወጣው፣ወይም ምላሱን በገመድ ልታስረው ትችላለህን?

2. መሰነጊያ በአፍንጫው ልታስገባ፣ወይም ጒንጩን በሜንጦ ልትበሳ ትችላለህን?

3. እርሱ እንድትምረው ይለማመጥሃል?በለስላሳ ቃላትስ ይናገርሃል?

4. ለዘላለም ባሪያ ታደርገው ዘንድ፣ከአንተ ጋር ይዋዋላልን?

5. እንደ ወፍ አልምደኸው ከእርሱ ጋር ልትጫወት ትችላለህ?ወይስ ለሴት አገልጋዮችህ መጫወቻነት ታስረዋለህን?

6. ነጋዴዎችስ በእርሱ ላይ ይከራከራሉን?ለቸርቻሪዎችስ ያከፋፍሉታል?

ኢዮብ 41