ኢዮብ 38:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰለት፤ እንዲህም አለው፤

2. “ዕውቀት በጐደለው ቃል፣ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማን ነው?

3. እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ ልጠይቅህ፣አንተም መልስልኝ።

4. “ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ?በእርግጥ የምታስተውል ከሆንህ፣ ንገረኝ።

ኢዮብ 38