ኢዮብ 36:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. አሁን ግን ለክፉዎች የሚገባው ፍርድ በላይህ ተጭኖአል፤ፍርድና ብይን ይዘውሃል።

18. ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ።

19. ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን?

20. ሰዎች ከቤታቸው የሚወሰዱበትን፣ሌሊት አትመኝ።

ኢዮብ 36