ኢዮብ 34:27-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. እርሱን ከመከተል ተመልሰዋልና፤መንገዱንም ችላ ብለዋል።

28. የድኾች ልቅሶ ወደ እርሱ እንዲደርስ ሰበብ ሆኑ፤የመከረኞችን ጩኽት ሰማ።

29. እርሱ ዝም ቢል፣ ማን ሊወቅሰው ይችላል?ፊቱንስ ቢሰውር፣ ማን ሊያየው ይችላል?እርሱ ከሰውም፣ ከሕዝብም በላይ ነው፤

30. ይህም የሆነው ዐመፀኛው ሕዝቡን እንዳይገዛ፣ወጥመድም በፊታቸው እንዳይዘረጋ ነው።

ኢዮብ 34