ኢዮብ 34:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. በእውነት እግዚአብሔር ክፋትን አይሠራም፤ሁሉን የሚችል አምላክ ፍትሕን አያጣምምም።

13. ምድርን እንዲገዛ የሾመው አለን?የዓለምስ ሁሉ ባለቤት ያደረገው ማን ነው?

14. እርሱ መንፈሱን መልሶ ቢወስድ፣እስትንፋሱንም ወደ ራሱ ቢሰበስብ፣

15. ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት በጠፋ፣ሰውም ወደ ዐፈር በተመለሰ ነበር።

16. “ማስተዋል ካለህ ይህን ስማ፤እኔ የምለውንም አድምጥ።

ኢዮብ 34