ኢዮብ 3:19-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ትንሹም ትልቁም በዚያ ይገኛል፤ባሪያው ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።

20. “በመከራ ላሉት ብርሃን፣ነፍሳቸው ለተማረረች ሕይወት ለምን ተሰጠ?

21. ሞትን በጒጒት ለሚጠብቁና ለማያገኙት፣ከተሰወረ ሀብት ይልቅ ለሚሹት፣

22. ወደ መቃብር ሲቃረቡ ደስ እያላቸው፣በሐሤት ለሚሞሉ ሕይወት ለምን ተሰጠ?

23. መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፤እግዚአብሔርም በዐጥር ላጠረው፣ሕይወት ለምን ተሰጠ?

24. ትካዜ ምግብ ሆኖኛልና፤የሥቃይ ጩኸቴም እንደ ውሃ ይፈሳል።

ኢዮብ 3