ኢዮብ 29:16-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ለችግረኛው አባት፣ለባይተዋሩ ተሟጋች ነበርሁ።

17. የኀጢአተኛውን ክራንቻ ሰበርሁ፤የነጠቀውንም ከጥርሶቹ አስጣልሁ።

18. “እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ ‘ዘመኔ እንደ አሸዋ በዝቶ፣በቤቴ ተደላድዬ እሞታለሁ፤

19. ሥሬ ወደ ውሃ ይዘረጋል፤ጠልም በቅርንጫፌ ላይ ያድራል፤

ኢዮብ 29