ኢዮብ 25:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ሰራዊቱ ሊቈጠር ይችላልን?ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?

4. ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፣ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ ይችላልን?

5. በፊቱ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፣ከዋክብትም ንጹሓን ካልሆኑ፣

6. ይልቁን ከብል የሚቈጠር የሰው ልጅ፣ትል የሆነውማ ሰው ምንኛ ያንስ!”

ኢዮብ 25