5. በምድረ በዳ እንዳሉ የሜዳ አህዮች፣ድኾች ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ፤ከበረሓው ምድር ለልጆቻቸው ምግብ ይሻሉ።
6. ከሜዳ መኖ ይሰበስባሉ፤ከክፉዎች የወይን ቦታም ይቃርማሉ።
7. ዕራቍታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፤በብርድም ጊዜ የሚለብሱት የላቸውም።
8. ከተራራ በሚወርድ ዝናብ በስብሰዋል፤መጠለያ አጥተው ቋጥኝ ዐቅፈዋል።
9. አባት የሌለው ልጅ ከዕቅፍ ተነጥቋል፤የድኻውም ልጅ በዕዳ ተይዞአል።
10. ዕራቍታቸውን ያለ ልብስ ይሄዳሉ፤ነዶ ይሸከማሉ፤ ግን ይራባሉ።