ኢዮብ 24:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ድርቅና ሙቀት የቀለጠውን በረዶ ከቦታው እንደሚያስወግድ፣ሲኦልም ኀጢአተኞችን ትነጥቃለች።

20. የተሸከመቻቸው ማሕፀን ትረሳቸዋለች፤ትል ይቦጠቡጣቸዋል፤ክፉዎች እንደ ዛፍ ይሰበራሉ፤የሚያስታውሳቸውም የለም።

21. የማትወልደውን መካኒቱን ይቦጠቡጣሉ፤ለመበለቲቱም አይራሩም።

22. ነገር ግን እግዚአብሔር ብርቱዎችን በኀይሉ ጐትቶ ይጥላል፤ቢደላደሉም የሕይወት ዋስትና የላቸውም።

ኢዮብ 24