ኢዮብ 22:5-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ክፋትህ ታላቅ፣ኀጢአትህ ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?

6. ያለ አንዳች ምክንያት ከወንድሞችህ መያዣ ወስደሃል፤ሰዎችን ገፈህ፣ ያለ ልብስ ዕራቍታቸውን አስቀርተሃል።

7. የዛሉትን ውሃ አላጠጣህም፤የተራቡትንም ምግብ ከልክለሃል።

8. ባለ ርስትና ኀያል፣በእርሱም የምትኖር ክቡር ሰው ብትሆንም፣

9. መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰደሃል፤የድኻ ዐደጎችንም ክንድ ሰብረሃል።

10. ድንገተኛ አደጋ ያናወጠህ፤ወጥመድም ዙሪያህን የከበበህ ለዚህ ነው።

11. እንዳታይ ጨለማ የሆነብህ፣ጐርፍም ያጥለቀለቀህ ለዚህ ነው።

ኢዮብ 22