ኢዮብ 22:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን የሚችለውን አምላክ ምን ደስ ታሰኘዋለህ?መንገድህ ያለ ነቀፋ ቢሆንስ የሚተርፈው ምንድን ነው?

4. “እርሱ የሚገሥጽህ፣ፍርድ ቤትም የሚያቀርብህ ስለምትፈራው ነውን?

5. ክፋትህ ታላቅ፣ኀጢአትህ ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?

6. ያለ አንዳች ምክንያት ከወንድሞችህ መያዣ ወስደሃል፤ሰዎችን ገፈህ፣ ያለ ልብስ ዕራቍታቸውን አስቀርተሃል።

ኢዮብ 22