ኢዮብ 21:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ኀጢአተኞች ለምን በሕይወት ይኖራሉ?ለምን ለእርጅና ይበቃሉ? ለምንስ እያየሉ ይሄዳሉ?

8. ዘራቸው በዐይናቸው ፊት፣ልጆቻቸውም በዙሪያቸው ጸንተው ሲኖሩ ያያሉ፤

9. ቤታቸው ያለ ሥጋት በሰላም ይኖራል፤የእግዚአብሔርም በትር የለባቸውም።

10. ኮርማቸው ዘሩ በከንቱ አይወድቅም፤ያስረግዛል፤ ላማቸውም ሳትጨነግፍ ትወልዳለች።

11. ልጆቻቸውን እንደ በግ መንጋ ያሰማራሉ፤ሕፃናታቸውም ይቦርቃሉ።

ኢዮብ 21