ኢዮብ 21:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እናንተ፣ ‘እግዚአብሔር የሰውን ቅጣት ለልጆቹ ያከማቻል’ ትላላችሁ፤ነገር ግን ያውቀው ዘንድ ለሰውየው ለራሱ ይክፈለው፤

20. ዐይኖቹ የራሱን ውድቀት ይዩ፤ሁሉን ከሚችል አምላክ ቍጣ ይጠጣ።

21. ሰው ወራቱ በተገባደደ ጊዜ፣ለቀሪ ቤተ ሰቡምን ይገደዋል?

22. “ከፍ ባሉት ላይ ለሚፈርድ አምላክ፣ዕውቀትን ሊያስተምረው የሚችል አለን?

ኢዮብ 21