ኢዮብ 20:15-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. የዋጠውን ሀብት ይተፋል፤እግዚአብሔርም መልሶ ከሆዱ ያወጣዋል።

16. የእባብ መርዝ ይጠባል፤የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል።

17. ማርና ቅቤ በሚያፈሱ ጅረቶች፣በወንዞችም አይደሰትም።

18. የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤

19. ድኾችን በመጨቈን ባዶአስቀርቶአቸዋልና፣ ያልሠራውንም ቤት ነጥቆአል።

20. “ክፉ ምኞቱ ዕረፍት አይሰጠውምሀብቱም ሊያድነው አይችልም።

21. ያለውን አሟጦ ስለሚበላ፣ዘላቂ ብልጽግና አይኖረውም።

22. በተድላ መካከል እያለ ጒስቍልና ይመጣበታል፤በከባድ መከራም ይዋጣል።

ኢዮብ 20