ኢዮብ 18:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. መቅሠፍት ሊውጠው ቀርቦአል፤ጥፋትም የእርሱን ውድቀት ይጠባበቃል።

13. ደዌ ቈዳውን ይበላል፤የሞት በኵርም ቅልጥሙን ይውጣል።

14. ተማምኖ ከሚኖርበት ድንኳን ይነቀላል፤ወደ ድንጋጤም ንጉሥ ይነዳል።

15. ድንኳኑ በእሳት ይያያዛል፤በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።

16. ሥሩ ከታች ይደርቃል፤ቅርንጫፉም ከላይ ይረግፋል።

ኢዮብ 18