ኢዮብ 17:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ቅኖች በዚህ ነገር ይደነግጣሉ፤ንጹሓንም በዐመፀኞች ላይ ይነሣሉ።

9. ጻድቃን ግን በያዙት መንገድ ይጸናሉ፤ንጹሕ እጅ ያላቸውም እየበረቱ ይሄዳሉ።

10. “ነገር ግን እናንተ ሁላችሁ፣ እስቲ ተመልሳችሁ እንደ ገና ሞክሩ!ከመካከላችሁ አንድም ጠቢብ አላገኝም።

11. ዕድሜዬ አለቀ፤ ዕቅዴም ከሸፈ፤የልቤም ሐሳብ ከንቱ ሆነ።

12. እነዚህ ሰዎች ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ጨልሞም እያዩ፣ ‘ብርሃን ቀርቦአል’ ይላሉ።

ኢዮብ 17