6. “እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ መተረቻ፣ፊቱ ላይ የሚተፋበት ሰውም አደረገኝ።
7. ዐይኔ ከሐዘን የተነሣ ፈዘዘ፤መላ አካሌም እንደ ጥላ ሆነ።
8. ቅኖች በዚህ ነገር ይደነግጣሉ፤ንጹሓንም በዐመፀኞች ላይ ይነሣሉ።
9. ጻድቃን ግን በያዙት መንገድ ይጸናሉ፤ንጹሕ እጅ ያላቸውም እየበረቱ ይሄዳሉ።
10. “ነገር ግን እናንተ ሁላችሁ፣ እስቲ ተመልሳችሁ እንደ ገና ሞክሩ!ከመካከላችሁ አንድም ጠቢብ አላገኝም።
11. ዕድሜዬ አለቀ፤ ዕቅዴም ከሸፈ፤የልቤም ሐሳብ ከንቱ ሆነ።