ኢዮብ 15:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ጠቢባን ከአባቶቻቸው የተቀበሉትን፤ሳይሸሽጉ የተናገሩትን አስረዳሃለሁ፤

19. ምድሪቱ ለአባቶቻቸው ተሰጠች፤በመካከላቸውም ባዕድ አልተቀመጠም፤

20. ክፉ ሰው ዕድሜውን ሙሉ፣ጨካኙም በተመደበለት ዘመን ሁሉ ይሠቃያል።

21. የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ላይ ይጮኻል፤በሰላም ጊዜ ቀማኞች አደጋ ያደርሱበታል።

22. ከጨለማ ወጥቶ ማምለጥ ይፈራል፤ለሰይፍም የተመደበ ነው።

ኢዮብ 15