ኢዮብ 15:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. የእግዚአብሔር ማጽናናት፣በርጋታ የተነገረህ ቃል አነሰህን?

12. ልብህ ለምን ይሸፍታል?ዐይንህንስ ምን ያጒረጠርጠዋል?

13. በእግዚአብሔር ላይ እንድትቈጣ፣እንደዚህ ያለ ቃል ከአፍህ እንዲወጣ ያደረገህ ምንድን ነው?

14. “ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ጻድቅስ ይሆን ዘንድ፣ ከሴት የተወለደ ምንድን ነው?

ኢዮብ 15