ኢዮብ 15:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ቴማናዊው ኤልፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ጠቢብ ሰው በከንቱ ንግግር መልስ ይሰጣልን?ወይስ በምሥራቅ ነፋስ ሆዱን ይሞላል?

3. በማይረባ ቃል፣ፍሬ ቢስ በሆነም ንግግር ይከራከራልን?

4. አንተ ግን እግዚአብሔርን መፍራት ታጣጥላለህ፤አምልኮተ እግዚአብሔርን ትከለክላለህ።

5. ኀጢአትህ አፍህን ታስተምረዋለች፤የተንኰለኞችንም አነጋገር መርጠህ ትይዛለህ።

ኢዮብ 15