ኢዮብ 12:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እግዚአብሔርን ጠርቼ የመለሰልኝ ሰው ብሆንም፣ለባልንጀሮቼ መሣቂያ ሆኛለሁ፤ጻድቅና ያለ ነቀፋ ሆኜ እያለሁ፣ መሣቂያ ሆኛለሁ።

5. የደላቸው በመከራ ያፌዛሉ፤እግሩ የተንሸራተተውንም ይገፈትራሉ።

6. የቀማኞች ድንኳን አይታወክም፤አምላካቸውን በእጃቸው ይዘው እየዞሩም፣እግዚአብሔርንም እያስቈጡ በሰላም ይኖራሉ።

ኢዮብ 12