ኢዮብ 12:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. እርሱ ያፈረሰውን መልሶ የሚገነባ የለም፣እርሱ ያሰረውን የሚፈታ አይገኝም።

15. እርሱ ውሃን ቢከለክል፣ ድርቅ ይሆናል፤ቢለቀውም ውሃው ምድሪቱን ያጥለቀልቃል።

16. ብርታትና ድል ማድረግ በእርሱ ዘንድ ይገኛል፤አታላዩም ተታላዩም በእርሱ እጅ ናቸው።

17. አማካሪዎችን ከጥበባቸው ያራቍታል፤ፈራጆችንም ማስተዋል ይነሣል።

18. ነገሥታትን ድግ ያስፈታል፤ገመድም በወገባቸው ያስራል።

ኢዮብ 12