ኢዮብ 10:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ዘመንህ እንደ ሟች ሰው ዘመን ነውን?ወይስ ዓመታትህ እንደ ሰው ዓመታት ናቸውን?

6. ታዲያ፣ በደልን የምትፈላልግብኝ፣ኀጢአቴንም የምትከታተለው ለምንድን ነው?

7. እኔ በደለኛ እንዳልሆንሁ፣ከእጅህም ሊያስጥለኝ ማንም እንደማይችል አንተ ታውቃለህ።

8. “እጅህ አበጀችኝ፤ ሠራችኝም፤መልሰህ ደግሞ ታጠፋኛለህን?

ኢዮብ 10