ኢያሱ 6:25-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ኢያሪኮን እንዲሰልሉ ኢያሱ የላካቸውን ሰዎች ስለ ደበቀች፣ ጋለሞታዪቱን ረዓብን፣ ቤተ ሰቧንና የእርሷ የሆኑትን ሁሉ አዳናቸው፤ እርሷም እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤላውያን መካከል ትኖራለች።

26. በዚያን ጊዜም ኢያሱ፣ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ይህችን ከተማ መልሶ የሚሠራት ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን፤“መሠረቷን ሲጥል፣የበኵር ልጁ ይጥፋ፤ቅጥሮቿንም ሲያቆም፣የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ” ብሎ ማለ።

27. ስለዚህ እግዚአብሔር ከኢያሱ ጋር ነበር፤ ዝናውም በምድሪቱ ሁሉ ላይ ወጣ።

ኢያሱ 6