ኢያሱ 22:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚህ ጊዜ ኢያሱ የሮቤልንና የጋድን ነገዶች፣ እንዲሁም የምናሴን ነገድ እኩሌታ ጠርቶ፣

2. እንዲህ አላቸው፤ “የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ያዘዘውን ሁሉ ጠብቃችኋል፤ እኔም ያዘዝኋችሁን በሙሉ ፈጽማችኋል፤

3. ከረጅም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ወንድሞቻችሁን አልተዋችሁም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ተልእኮ በሚገባ ተወጥታችኋል።

4. አሁንም አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ወንድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ ርስት አድርጎ በሰጣችሁ ምድር ወዳለው ቤታችሁ ተመለሱ።

ኢያሱ 22