9. የይሁዳ ነገድ የያዘው ርስት እጅግ ሰፊ ስለ ነበር፣ ከይሁዳ ነገድ ድርሻ ተከፍሎ ለስምዖን ነገድ በርስትነት ተሰጠ፤ ከዚህ የተነሣም የስምዖን ነገድ በይሁዳ ነገድ ድርሻ ርስት ሊካፈል ቻለ።
10. ሦስተኛው ዕጣ ለዛብሎን ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤የርስታቸውም ድንበር እስከ ሣሪድ ይደርሳል፤
11. ወደ ምዕራብም በመሄድ በመርዓላ በኩል ያልፋል፤ ደባሼትን ተጠግቶም በዮቅንዓም አጠገብ እስካለው ወንዝ ድረስ ይዘልቃል።
12. ከሣሪድም ወደ ምሥራቅ በመታጠፍ፣ የፀሓይ መውጫ ወደ ሆነው አገር ወደ ኪስሎትታቦር በመዝለቅ እስከ ዳብራት ሄዶ ወደ ያፊዓ ያቀናል፤
13. ከዚያም ወደ ምሥራቅ በመቀጠል፣ ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒትቃጺን ይዘልቃል፤ ከዚያ ደግሞ ወደ ሪሞን በመሄድ፣ ወደ ኒዓ ይታጠፋል።
14. በስተ ሰሜንም በኩል ወደ ሐናቶን ይዞርና በይፍታሕኤል ሸለቆ ላይ ይቆማል።
15. ደግሞም ቀጣትን፣ ነህላልን፣ ሺምሮንን፣ ይዳላንና ቤተ ልሔምን ይጨምራል፤ እነዚህም ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው።
16. እነዚህ ሁሉ ለዛብሎን ነገድ ርስት ሆነው ለየጐሣ ለየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።
17. አራተኛው ዕጣ ለይሳኮር ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤
18. ምድራቸውም የሚከተሉትን ያካትታል፤ኢይዝራኤል፣ ከስሎት፣ ሱነም፣
19. ሐፍራይም፣ ሺኦን፣ አናሐራት፣
20. ረቢት፣ ቂሶን፣ አቤጽ፣
21. ሬሜት፣ ዐይንጋኒም፣ ዐይንሐዳ እንዲሁም ቤትጳጼጽ።
22. ድንበራቸውም ታቦርና፣ ሻሕጹማን፣ ቤትሳሚስን ይነካና በዮርዳኖስ ላይ ያቆማል፤ እነዚህ ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ ስድስት ከተሞች ናቸው።
23. እነዚህ ለይሳኮር ነገድ ርስት ሆነው ለየጐሣ ለየጐሣው የተደለደሉ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ።