ኢያሱ 15:61-63 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

61. በምድረ በዳው ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ቤትዓረባ፣ ሚዲን፣ ስካካ፣

62. ኒብሻን፣ የጨው ከተማና ዓይንጋዲ፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።

63. ነገር ግን የይሁዳ ዘሮች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከቦታቸው ሊያስለቅቋቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በኢየሩሳሌም አብረው ይኖራሉ።

ኢያሱ 15