17. ስለዚህ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዛት፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት።
18. ዓክሳ ወደ ጎቶንያል በመጣች ጊዜም፣ ከአባትዋ ላይ የእርሻ መሬት እንዲለምን አጥብቃ ነገረችው። ከአህያዋ ላይ እንደ ወረደች ካሌብ፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት።
19. እርስዋም፣ “እባክህ፤ በጎ ነገር አድርግልኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ጉድጓዶች ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።
20. ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነው፤
21. በኔጌብ አካባቢ በኤዶም ድንበር ላይ በወሰኑ ጫፍ የሚገኙት የይሁዳ ነገድ ደቡባዊ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ቀብስኤል፣ ዔዴር፣ ያጉር፣
22. ቂና፣ ዲሞና፣ ዓድዓዳ፣
23. ቃዴስ፣ ሐጾር፤ ዩትናን፣
24. ዚፍ፣ ጤሌም፣ በዓሎት፣
25. ሐጾርሐዳታ፣ ሐጾር የምትባለው ቂርያትሐጾር
26. አማም፣ ሽማዕ፣ ሞላዳ፣
27. ሐጻርጋዳ፣ ሐሽሞን፣ ቤትጳሌጥ፣
28. ሐጸር ሹዓል፣ ቤርሳቤህ፣ ቢዝዮትያ
29. በኣላ፣ ዒዪም፣ ዓጼም፣
30. ኤልቶላድ፣ ኪሲል፣ ሔርማ፣
31. ጺቅላግ፣ ማድማና፣ ሳንሳና
32. ልባዎት፣ ሺልሂም፣ ዓይንና ሪሞን ናቸው፤ ባጠቃላይም ከተሞቹና መንደሮቻቸው ሃያ ዘጠኝ ናቸው።
33. በምዕራቡ በኰረብታዎች ግርጌ ያሉት ደግሞ እነዚህ ናቸው፤ ኤሽታኦል፤ ጾርዓ፣ አሽና
34. ዛኖዋ፣ ዓይንገኒም፣ ታጱዋ፣ ዓይናም፣
35. የርሙት፣ ዓዶላም፣ ሰኰት፣ ዓዜቃ፣
36. ሽዓራይም፣ ዓዲታይም፣ ግዴራ፣ ግዴሮታይም ናቸው፤ ከተሞቹም ከነ መንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ናቸው።