ኢሳይያስ 9:13-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።

14. ስለዚህ እግዚአብሔር ራስንና ጅራትን፣የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸምበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።

15. ሽማግሌዎችና የተከበሩ ሰዎች ራስ፣ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ደግሞ ጅራት ናቸው።

16. ይህን ሕዝብ የሚመሩት ያስቱታል፤የሚመራውም ሕዝብ ከመንገድ ወጥቶ ይባዝናል።

17. ስለዚህ ጌታ በጐበዛዝት ደስ አይሰኝም፤አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረ በትና ክፉ አድራጊ ነው፤የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና።ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

ኢሳይያስ 9