ኢሳይያስ 9:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ነገር ግን እግዚአብሔር የረአሶንን ጠላቶች ያጠናክራል፤በእነርሱም ላይ ያመጣባቸዋል፤ባለጋራዎቻቸውንም ያነሣሣባቸዋል።

12. ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫ ጭቋታል።ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤እጁ እንደ ተዘረጋ ነው።

13. ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።

14. ስለዚህ እግዚአብሔር ራስንና ጅራትን፣የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸምበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።

ኢሳይያስ 9