ኢሳይያስ 8:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤እያጥለቀለቀ ያልፋል፤እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤አማኑኤል ሆይ፤የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከዳር ይሸፍናሉ።”

9. እናንተ አሕዛብ፣ ፎክሩ፤ግን ደንግጡ።በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ፤ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤

10. ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።

11. እግዚአብሔር ብርቱ እጁን በላዬ አድርጎ የእነዚህን ሰዎች መንገድ እንዳልከተል አስጠነቀቀኝ፤ እንዲህም አለኝ፤

12. “እነዚህ ሰዎች፣ ‘አድማ’ ብለው የሚጠሩትን፣ማንኛውንም ነገር፣ ‘አድማ’ አትበሉ፤እነርሱ የሚፈሩትን አትፍሩ፤አትሸበሩለትም።

ኢሳይያስ 8