6. “ይሁዳን እንውረር፤ እንበታትነው ተከፋፍለንም እንግዛው፤ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥባት።”
7. ልዑል እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፦“ ‘ይህ ምክራቸው አይፈጸምም፤ከቶም አይደረግም፤
8. የሶርያ ራስ ደማስቆ፣የደማስቆ ራስ ረአሶን ነውና፤በሥልሳ አምስት ዓመት ውስጥ፣የኤፍሬም ሕዝብ ይበታተናል፤ ሕዝብመሆኑም ይቀራል።
9. የኤፍሬም ራስ ሰማርያ፣የሰማርያም ራስ የሮሜልዩ ልጅ ነው።እንግዲህ በእምነታችሁ ካልጸናችሁ፣ፈጽሞ መቆም አትችሉም።’ ”
10. እንደ ገናም እግዚአብሔር አካዝን እንዲህ አለው፤