ኢሳይያስ 7:5-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ሶርያ ኤፍሬምና፣ የሮሜልዩ ልጅ ሊያጠፉህ እንዲህ ብለው ተማከሩ፤

6. “ይሁዳን እንውረር፤ እንበታትነው ተከፋፍለንም እንግዛው፤ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥባት።”

7. ልዑል እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፦“ ‘ይህ ምክራቸው አይፈጸምም፤ከቶም አይደረግም፤

8. የሶርያ ራስ ደማስቆ፣የደማስቆ ራስ ረአሶን ነውና፤በሥልሳ አምስት ዓመት ውስጥ፣የኤፍሬም ሕዝብ ይበታተናል፤ ሕዝብመሆኑም ይቀራል።

9. የኤፍሬም ራስ ሰማርያ፣የሰማርያም ራስ የሮሜልዩ ልጅ ነው።እንግዲህ በእምነታችሁ ካልጸናችሁ፣ፈጽሞ መቆም አትችሉም።’ ”

10. እንደ ገናም እግዚአብሔር አካዝን እንዲህ አለው፤

11. “ከጥልቁ ጥልቅ ወይም ከከፍታው ከፍታ ምልክት እንዲሰጥህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ለምን።”

12. አካዝ ግን፣ “አልለምንም፣ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም” አለ።

13. ኢሳይያስም እንዲህ አለ፤ “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፤ ስሙ፤ የሰውን ትዕግሥት መፈታተናችሁ አንሶ የአምላኬን ትዕግሥት ትፈታተናላችሁን?

ኢሳይያስ 7