ኢሳይያስ 64:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆኑ፤ጽዮን ራሷ እንኳ ምድረ በዳ፣ ኢየሩሳሌምም የተፈታች ሆናለች።

11. አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰውና የተከበረው ቤተ መቅደሳችን፣በእሳት ተቃጥሎአል፤ያማሩ ቦታዎቻችንም ሁሉ እንዳልነበር ሆነዋል።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ አትመለስምን?ዝም ብለህ ከልክ በላይ ትቀጣናለህን?

ኢሳይያስ 64