ኢሳይያስ 63:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. መንግሥታትን በቍጣዬ ረጋገጥሁ፤በመዓቴም አሰከርኋቸው፤ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስሁ።”

7. የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ እግዚአብሔር ስላደረገልን ሁሉ፣ስለሚመሰገንበት ሥራው፣እንደ ፍቅሩና እንደ ቸርነቱ መጠን፣ለእስራኤል ቤት ያደረገውን፣አዎን፣ ስላደረገው መልካም ነገር እናገራለሁ።

8. እርሱም፣ “ርግጥ ነው፤ እነርሱ ሕዝቤ ናቸው፤የማይዋሹኝ ወንዶች ልጆቼ ናቸው” አለ።ስለዚህም አዳኝ ሆነላቸው።

9. በጭንቃቸው ሁሉ ተጨነቀ፤የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤በፍቅሩና በምሕረቱ ዋጃቸው፤በቀደመው ዘመን ሁሉ አነሣቸው፤ተሸከማቸውም።

ኢሳይያስ 63