ኢሳይያስ 61:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ለድኾች የምሥራች እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛል።ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ለምርኮኞች ነጻነትን፣ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል፤

2. የተወደደውን የእግዚአብሔርን ዓመት፣የአምላካችንንም የበቀል ቀን እንዳውጅ፣የሚያለቅሱትን ሁሉ እንዳጽናና ልኮኛል፤

ኢሳይያስ 61