8. “ርግቦች ወደ ጐጆአቸው እንደሚበሩ፣እንደ ደመና የሚጓዙ እነዚህ እነማን ናቸው?
9. በርግጥ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤እርሱ ክብሩን ስላጐናጸፈሽ፣ለእስራኤል ቅዱስ፣ ለእግዚአብሔር አምላክሽ ክብር፣ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽን፣ከነብራቸውና ከነወርቃቸው ለማምጣት፣የተርሴስ መርከቦች ቀድመው ይወጣሉ።
10. “ባዕዳን ቅጥሮችሽን ይሠራሉ፤ነገሥታቶቻቸው ያገለግሉሻል፤በቊጣዬ ብመታሽም፣ርኅራኄዬን በፍቅር አሳይሻለሁ።
11. በሮችሽ ምንጊዜም የተከፈቱ ይሆናሉ፤ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ አይዘጉም፤ይህም ሰዎች የመንግሥታትን ብልጥግና ወደ አንቺ እንዲያመጡ፤ነገሥታታቸውም በድል ወደ አንቺ እንዲገቡ ነው።